
ለመሆኑ ብርሃነ መዋ ማን ነው
ብርሃነ መዋ ማለት ኢትዮጵያ ካሏት ወርቃማ ልጆቿ ውስጥ አንዱ ነው፡፡ አቶ ብርሀነ የሀገር መሪ፣ አስተዋይ፣ የሀገር ጸጋ፣ ለኢትዮጵያ በክፉ ቀን ደራሽ፣ የኢትዮጵያን ደስታና መከራ ከጎኗ ቆሞ ሲጋራ የነበረ እና ከፖለቲካ ውስጥ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና እድገት ተቆርቋሪ እድሜውን ሙሉ ህዝቡን ሲያገለግል የኖረ የቁርጠኛ ቀን ልጅ ነው፡፡ ዛሬ እንደምናያቸው አንዳንድ የቅንጅት መሪዎች ከዳር ቆሞ የአሜሪካ ሃምበርገር ሆዳቸውን ሲነፋችው እና ከየቦታው ሰርቀውም ሆነ አታለው ያጠራቀሙት ገንዘብ መበተኛ ሲያጡ ወደ ፖለቲካው የዞረ ሰው አይደለም፡፡
ብርሀነ ከሰራተኛው፣ ከነጋዴው፣ ሀሙህራኑ፣ ከጋዚጠኛው፣ ከተማሪው እና ከላብ አደሩ ጋር አብሮ የኖረ በላቡ ኑሮውን የኖረ በጥረቱ እና በእውቀቱ ኢትዮጵያን የረዳ ትልቅ የኢትዮጵያ ልጅ ነው፡፡ ዛሬ ከዚህ ከአሜሪካም ሆነ ከአውሮፓ ያሉ ፈሪ የቅንጅት ባላስልጣናትም ሆኑ የወያኔ መሪዎች አንድ ላይ ቢጨፈለቁ እንኳ ብርነን መተካት ቀርቶ የእሱን የመጀመሪያ ስም ፊደል እንኳ አይወጣቸውም፡፡
ለመሆኑ የህን ያውቁ ኖሯል?
ዛሬ ብርሀነ የፈጠራቸው ፈጠራዎች ለተራው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት እንደሚጠቅሙ፡፡
ለመሆኑ ጭቁኑ የታክሲ ነጂ መኪናው ተስብሮ የመለዋወጫ እቃ የለም ተብሎ እሱን እና ቤተሰቡን የሚያስተረድርበት ታክሲው ሲቆም የት እንደሚሄድ ታውቃላችሁ?
ዛሬ አሮጌም ሆኑ ዘመናዊ የቢራ፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የስሚንቶ ፋብሪካዎች በመለዋወጫ እጥረት ሲኖራቸው እና ስራቸው ሊቆም ሲል የት እንደሚሄዱ ያውቃሉ?
አካለ ስንኩላን የሜሄጃ ክራንቻቸው ሲሰበርባቸው የት እንደሚሄዱ ያውቃሉ?
ለመሆኑ የአቶ ብርሀነ የስራ ውጤቶች የእያንዳንዱን የኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮ እንዳሸሻለስ ታውቃሉ ?
አቶ ብርሃነ ለነጋዴው፣ ለፋብሪካ ሰራተኛው፣ ለሹፌሩ፣ ለተማሪው፣ ለተመራማሪው በአጠቃላያ ለሀገራችን ያደረገው እገዛ ዘሬ ከዚህ ከአሜሪካ ሆነው ጉራቸውን ለሚነፉ የሩቅ ጀግኖች ጋር አብሮ መታየቱ በጣም ያሳዝናል፡፡ ዛሬ የአቶ ብርሀነ በስደት ላይ መሆነ የተጎዳችው ኢትዮጵያ ናት፡፡ የተጎዳው ህዝቡ ነው፡፡ አቶ ብርሀነ ሀገርን ህዝብን ለመምራት እና ለማደራጀት ብሎም ኢትዮጵያን ወደ ፊት ሊያራምድ የሚችል ታላቅ የሃገር ቅርስ ነው፡፡
አቶ ርብረሃነ ለኢትዮጵያ መሪነት የሚበቃ የተፈተነ በወሬ ሳይሆን በተግባር እድሜውን ሞሉ ስራውን ያሳየ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ የምትፈልገው እንደ አቶ በርሃነ እንደ አቶ ሀያሉ ሻውል፣ እንደ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ እና ዛሬ በእስር ቤት በመማመው ላይ ያሉትን ልጆቿን ነው፡፡
No comments:
Post a Comment