Tuesday, October 17, 2006

ብርሃነ መዋ ማን ነው?

ለመሆኑ ብርሃነ መዋ ማን ነው?


ብርሃነ መዋ ማለት ኢትዮጵያ ካሏጽርቃማ ልኮቿ ውስጥ አንዱ ነው፡፡ አቶ ብርሀነ የሀገር ሃበር ፈጣሪ፣ መሪ፣ አስተዋይ፣ የሀገር ጸጋ፣ ለኢትዮጵያ በክፉ ወቀን ደራሽ፣ የኢትዮጵያን ደስታና መከራ ከጎኗ ቆሞ ሲጋራ የነበረ እና ከፖለቲካ ውስጥ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና እድገት ተቆርቋሪ እድሜውን ሙሉ ህዝቡን ሲያገለግል የኖረ የቁርጠኛ ቀን ልጅ ነው፡፡ ዛሬ እንደምናያቸው አንዳንድ የቅንጅት መሪዎች ገዳር ቆመው የአሜሪካ ሃምበርገር ሆዳቸውን ሲነፋችው እና ከየቦታው ሰርቀውም ሆነ አታለው ያጠራቀሙት ገንዘብ መበተኛ ሲያጡ ወደ ፖለቲካው የዞረ ሰው አይደለም፡፡

ብርሀና ከሰራተኛው፣ ከነጋዴው፣ ሀሙህራኑ፣ ከጋዚጠኛው፣ ከተማሪው እና ከላብ አደሩ ጋር አብሮ የኖረ በላቡ ኑሮውን የኖረ በጥረቱ እና በእውቀቱ ኢትዮጵያን የረዳ ትልቅ የኢትዮጵያ ልጅ ነው፡፡ ዛሬ ከዚህ ከአሜሪካም ሆነ ከአውሮፓ ያሉ ፈሪ የቅንጅት ባላስልጣናትም ሆኑ የወያኔ መሪዎች አንድ ላይ ቢጨፈለቁ እንኳ ብርነን መተካት ቀርቶ የእሱን የመጀመሪያ ስም ብን እንኳ አይወጣቸውም፡፡ ለመሆኑ የህን ያውቁ ኖሯል፡፡

ዛሬ ብርሀነ የፈጠራቸው ፈጠራዎች ለተራው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት እንደሚጠቅሙ፡፡

ለመሆኑ ጭቁኑ የታክሲ ነጂ መኪናው ተስብሮ የመለዋወጫ እቃ የለም ተብሎ እሱን እና ቤተሰቡን የሚያስተረድርበት ታከሰቲው ሲቆም የት እንደሚሄድ ታውቃላች፡፡
ዛሬ በጣሊያን ጊዜ የተሰሩ አሮጌም ሆኑ ዘመናዊ የቢራ፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የዚሚንቶ ፋብሪካዎች በመለዋወጫ እትረት ስራቸው ሲቆም የት እንደሚሄዱ ያውቃሉ፡፡

አካለ ስንኩላን የሜሄጃ ክራንቻቸው ሲሰበርባቸው የት እንደሚሄዱ ያውቃሉ

ለመሆኑ የአቶ ብርሀነ የስራ ውጤቶች የእያንዳንዱን የኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮ እንዳሸሻለስ ታውቃሉ፡፡

አቶ ብርሃነ ለነጋዴው፣ ለፋብሪካ ሰራተኛው፣ ለሹፌሩ፣ ለተማሪው፣ ለተመራማሪው በአጠቃላያ ለሀገራችን ያደረገው እገዛ ዘሬ ከዚህ ከአሜሪካ ሆነው ጉራቸውን ለሚነፉ የሩቅ ጀግኖች ጋር አብሮ መታየቱ በጣም ያሳዝናል፡፡ ዛሬ የአቶ ብርሀነ በስደት ላይ መሆነ የተጎዳችው ኢትዮጵያ ናት፡፡ የተጎዳው ህዝቡ ነው፡፡ አቶ ብርሀነ ሀገርን ህዝብን ለመምራት እና ለማደራጀት ብሎም ኢትዮጵያን ወደ ፊት ሊያራምድ የሚችል ታላቅ የሃገር ቅርስ ነው፡፡

No comments: